የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች በማጥናት በመጠበቅና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ፡፡

በሀገርህን እወቅ ክበባት የተደራጁ የዞኑ የማኔጅመንት አካላትና የመንግስት ሰራተኞች ተንቀሳቅሰው በቡታጅራ ከተማና በሶዶ ወረዳ የሚገኙ አንዳንድ የቱሪዝም መስህቦችን ጉብኝተዋል፡፡ የጉራጌ ዞን ባህል፣ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅረአለም ከበደ በጉብኝቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ከሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት በየሴክተሩ የሀገርህን እወቅ ክበባትን በማቋቋም የቱሪዝም መስህቦችን የማስጎብኘት …

Continue reading…

ባህልና ቋንቋ በተገቢው በማልማት በመጠበቅና ለትውልድ ጠብቆ ማቆየት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ፡፡

የሴክተሩ የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃጸም ግምገማና የግንዛቤ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቅረአለም ከበደ እንዳስታወቁት ባህልና ቋንቋን በተገቢው በማልማትና በማስተዋወቅ ለቀጣይ ትውልድ ጠብቆ ለማቆየት በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡ የቋንቋና የባህል ሲምፖዚየም በማዘጋጀት የጉራግኛ ቋንቋና ባህልን ይበልጥ ለማጎልበት ወሳኝ እንደሆነና ቋንቋውን በየትምህርት …

Continue reading…

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ስብዕናው የተገነባ ወጣት በማፍራት የሀገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረት ድንጋይ የተጣለበት ስድስተኛ አመት በወልቂጤ ከተማ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች በድምቀት ተከበረ፡፡ እለቱን አስመልክቶ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ኮርንማ እንዳሉት አስተዳደራቸው ስብዕናው የተገነባ ወጣት በማፍራትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱ በማሳደግ የሀገሪቱ የህዳሴ ጉዞ ለማጠናከር እየሰራ ነው፡፡ የዞኑ ወጣት የግድቡ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት እለት ጀምሮ …

Continue reading…

ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደረገው ሽግግር በማፋጠን ሀገሪን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ ርብርብ እያደረገ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኢንዱስት ልማት ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከኢፌድሪ ንግድና ኢንዱስት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በዘርፉ ተሰማርተው ለሚሰሩ አመራሮች፣ ባለሙያችና ባለድርሻ አካላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ተሰጥቷል፡፡ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጌትነት በጋሻው ስልጠናውን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት በሀገራችን የተጀመረው የህዳሴ …

Continue reading…